Skip to Content

​News & media

ዜና

All news
፵፭ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ  ጉባኤ

ዜና

፵፭ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ

12 Oct 2026

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፵፭ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ዐዲሱ የጽርሐ ተዋሕዶ የስብሰባ ማዕከል ከጥቅምት ፫ - ፯ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መምሪያ የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን የሚያስችል የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና ተጠናቀቀ።

ዜና

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መምሪያ የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን የሚያስችል የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና ተጠናቀቀ።

12 Oct 2026

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መምሪያ የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን የሚያስችል የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና ተጠናቀቀ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ከአይሲቲና ዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ጋር ያዘጋጀው የሁለት ቀናት የሥልጠና የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና ተጠናቀቀ ። በሥልጠው የአህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጆች፣ የአይሲቲ ዋና ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች የተሳተፉ ሲሆን ፤ ሥልጠናው በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቁትን የአይሲቲ ፖሊሲና ስትራቴጂ ማስተዋወቅ፣ የሶፍትዌር ምንነት ለቤተክርስቲያኗ ዘመናዊ አሠራር ካለው ፋይዳ ጋር ማገናዘብ፣ እንዲሁም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና ዲጂታል ሚዲያ ቴክኖሎጂዎች በቤተክርስቲያኗ አገልግሎት ላይ የሚፈጥሯቸውን ዕድሎችና ተግዳሮቶች መመርመር ዋና ዓላማዎቹ አድርጓል። በሥልጠና መዝጊያ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ መጋቤ ጥበብ ሙሉዓለም ዐሥራት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የኢንፎርሜሽን እና ኮሚንኬሽን የመምርያ ኃላፊ እና የድርጅት ኃላፊዎች ፣ ቀሲስ ዮሐንስ ተስፋዬ የአማካሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ። ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ "ጥበብን ማግኘት ከወርቅ ይበልጣል" የሚለውን የመጽሐፍ ምሳሌ ኃሣብ በማንሳት ቅድስት ቤተክርስቲያን ዘመኑን መዋጀ አገልግሎት እንድትሰጥ የኢፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ሥልጠና እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል። በሥልጠናው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ለቤተክርስቲያን አገልግሎት፦ በወቅታዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ በተደረጉ ውይይቶችም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) በአግባቡ ከተጠቀምንበት ለዘመናዊ የሰነድ አያያዝ፣ ለፈጣን መረጃ ልውውጥ እና ለሰፊ ተደራሽነት ትልቅ ዕድል መሆኑ ተነስቷል። አጠቃቀሙም ለወደፊት በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ለሚጸድቁ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ግብአት እንደሚሆን ተመላክቷል። በሥልጠናው መርሐ ግብር ላይ በተለያዩ ምሁራን የቀረቡ ጥናቶች እና ሙያዊ ማብራሪያዎች ቀርበዋል። በሥልጠናዎቹ ዙሪያ ሙያዊ ውይይት ተከናውኗል ። በሥልጠናው መጨረሻ ቀሲስ ዮሐንስ ተስፋዬ በቀጣይ ትግበራ ላይ መመሪያ እና ኃሳብ ሰጥተዋል። የተግባር እቅድ ማውጣት፣ ያሉትን ክፍተቶች መሙላት፣ የመረጃ ጥራትን ማሻሻል፣ የአጠቃቀም መመሪያ ማውጣት፣ የደኅንነት ሥርዓት ማዘጋጀት፣ የሚድያ አጠቃቀምን ማሻሻል፣ የAI ስህተቶችን ማረም ፣ ክትትል እና ግምገማ ማድረግ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ገልጸዋል። ሥልጠናውን ተከትሎ ሁሉም ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር የቤተክርስቲያኗን አገልግሎት የሰለጠነና ዘመናዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል። መጋቤ ጥበብ ሙሉዓለም ዐሥራት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ኃላፊነቱን ከተረከቡ ጀምሮ በአይሲቲው ዘርፍ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የመልካም አስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋት በሰጡት መመሪያ መሠረት የቴክኖሎጂ ሥራዎች በጥንቃቄ ተጠብቀው እንዲቀጥሉ ተደርጓል ብለዋል። አክለውም ለቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎትና አስተዳደራዊ ሥራዎች ፈተና እየሆኑ ባሉ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) እና የዲጂታል ሚዲያ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ የመነሻ ውይይቶች በማድረግ ለወደፊት በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ለሚጸድቁ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ግብአት የሚሆኑ ሐሳቦች እንደሚሰባሰቡ አስረድተዋል፡፡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) በአግባቡ ከተጠቀምንበት ትልቅ ዕድል ሲሆን፣ ካልሆነ ግን ተጓዳኝ ችግሮች ስለሚመጡ አጠቃቀሙን በጥንቃቄ መረዳት ያስፈልጋል። በመሆኑም ከሥልጠናው በኋላ ሁሉም ባለሙያና ኃላፊ ወደ ተግባር በመቀየር የቤተክርስቲያኗን አገልግሎት የሰለጠነና ዘመናዊ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል። በመጨረሻም ለሥልጠናው ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና እና በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ቡራኬ ፤ መርሐ ግብሩ በጸሎት ተጠናቋል ። የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/

ተጨማሪ ያንብቡ
ዓለም አቀፍ የጉባኤ ማዕከል ተመረቀ

ዜና

ዓለም አቀፍ የጉባኤ ማዕከል ተመረቀ

12 Oct 2026

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ያስገነባው ዓለም አቀፍ የጉባኤ ማዕከል በተመረቀበት መርሐ ግብር ላይ ቃለ ቡራኬና በረከት አስተላልፈዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ

Important features

One portal. Every Church gateway.

Discover parishes, explore dioceses, request services, and learn from Church knowledge — all in one living digital home for the faithful.

አንድ ፖርታል · ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶች

Knowledge library

04

Knowledge library

የእውቀት ቤተ መጻሕፍት

Read published writings, teaching resources and public knowledge of the Church.

Open the library