Skip to Content

ዜና

የጽርሐ ተዋሕዶ ዓለም ዓቀፍ የጉባኤ ማዕከል የቤተ ክርስቲያናችንን ታሪካዊ የልማትና የዕድገት ጉዞ የሚያንጸባርቅ፥ በቴክኖሎጂ አደረጃጀቱና በግንባታ ጥራቱ የላቀ ዘመናዊ ቅርስ ነው ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ገለጹ።

የኢኦተቤ መገናኛ · 19 Oct 2026 · 1 ደቂቃ ንባብ

የጽርሐ ተዋሕዶ ዓለም ዓቀፍ የጉባኤ ማዕከል የቤተ ክርስቲያናችንን ታሪካዊ የልማትና የዕድገት ጉዞ የሚያንጸባርቅ፥ በቴክኖሎጂ አደረጃጀቱና በግንባታ ጥራቱ የላቀ ዘመናዊ ቅርስ ነው ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ገለጹ።

የጽርሐ ተዋሕዶ ዓለም ዓቀፍ የጉባኤ ማዕከል የቤተ ክርስቲያናችንን ታሪካዊ የልማትና የዕድገት ጉዞ የሚያንጸባርቅ፥ በቴክኖሎጂ አደረጃጀቱና በግንባታ ጥራቱ የላቀ ዘመናዊ ቅርስ ነው ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ገለጹ።
ዘጋቢ ሰላም አምባዬ
(#EOTCTV ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለዘመናት ሲገነባ የቆየውን ''ጽርሐ ተዋሕዶ ዓለም ዓቀፍ የጉባኤ ማዕከል ተብሎ የተሰየመው ዘመናዊ የጉባኤ ማዕከል ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ተመርቋል።
በምረቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የዓለም ዓቀፉ የጉባኤ ማዕከል ግንባታ ለፍጻሜው ሊበቃ የቻለው በየዘመናቱ የተተኩ ቅዱሳን ፓትርያርኮች እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ባደረጉት ያልተቋረጠ ክትትልና አባታዊ አመራር መሆኑን በሕንጻው ምርቃት ላይ በስፋት
ተገልጿል ።
በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራአስኪያጅ ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ይህ ታሪካዊ ፕሮጀክት የቤተ ክርስቲያኗን መንፈሳዊ፣ ተቋማዊና ማኅበራዊ አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ታስቦ የተገነባ ሲሆን፤ የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛና አስቸኳይ ጉባኤያትን፣ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤዎችን፣ የእህት አብያተ ክርስቲያናትንና የዓለም አቀፍ ሃይማኖታዊ ተቋማት የጋራ ስብሰባዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ በብቃት የማስተናገድ አቅም እንዳለው ገልጸዋል ።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በንግግራቸው አዳራሹ ከስብሰባ አዳራሽነቱ ባሻገር ለልዩ ልዩ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ ኩነቶች የሚውሉ ዘመናዊ ቢሮዎችን፣ ያካተተ መሆኑን የጠቆሙ ሲሆን፤ ለተኪው ትውልድ የሚሻገር ዘላቂ ቅርስ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑንም አክለዋል ።
በተጨማሪም የጉባኤው ማእከል ከስብሰባ አዳራሽነት ባሻገር ለልዩ መንፈሳዊ፥ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኩነቶች የሚውሉ ዘመናዊ ቢሮዎችን፥ አነስተኛ የስብሰባ ክፍሎች እና ጥናታዊ ሲምፖዚየሞች የሚካሄዱባቸውን መድረኮችና ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎችን ያካተተ ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጥ ነው ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።
የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/ See less

ተዛማጅ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ አዲሱን ሁለገብ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ጎበኙ፡፡

ዜና

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ አዲሱን ሁለገብ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ጎበኙ፡፡

19 Oct 2026

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር አዲሱን ሁለገብ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ጎበኙ፡፡ መስከረም ፳፱ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የተገነባው አዲሱ ዘመናዊ ዓለም አቀፍ ሁለገብ የሰብሰባ ማዕከል የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች አርቆ አሳቢነት የሚያሳይ፣ ለቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለሀገር ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ ማዕከል ነው፡፡ ይህን ግዙፍ ሕንጻ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር አዲሱን ሁለገብ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ጎብኝተዋል፡፡ ይህ ዓለም አቀፋዊ ጥራትና ውበት የተላበሰው ሕንጻ በሚገባ ተሠርቶ እንዲጠናቀቅ ያደረጉት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡ በሕንጻው ዙሪያ በቂ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራ እንዲኖር፥ ቅጽረ ግቢው ቤተ ክርስቲያንን በሚገልጽ ሥነ ጥበብ እንዲያጌጥ ተደርጎ የተሠራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በምሕንድስና ባለሙያዎቹ እንደተገለጸው ዓለም አቀፍ ሁለገብ ሕንጻ ከ2‚260 በላይ ተሰብሳቢዎችን የማስተናገድ አቅም ያለው አዳራሽ፥ ሌሎች አነስተኛ የስብሰባና የሥልጠና አዳራሾች፣ ከአንድ መቶ በላይ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን የሚይዝ የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ፥ ሙዚየምና ዲጂታል ቤተ መጻሕፍት፣ ቢሮዎች፣ ዘመናዊ ሬስቶራንትና ለሌሎችም አገልግሎት የሚሰጥ ክፍሎችን የያዘ ተገልጿል፡፡ አዲሱን ሁለገብ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ጥቅምት ፩ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም የሚመረቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/ See less

ተጨማሪ ያንብቡ
የቅዱሳን ፓትርያርኮች እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መታሰቢያ ጸሎት

ዜና

የቅዱሳን ፓትርያርኮች እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መታሰቢያ ጸሎት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተካሄደ፡፡

18 Oct 2026

የቅዱሳን ፓትርያርኮች እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መታሰቢያ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከብሯል፡፡ የቅዱሳን ፓትርያርኮች እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መታሰቢያ ቀን ሥነ ሥርዐት ላይ በቁጥር በጣም አነስተኛ ሰው የተገኘበት ነበር፡፡ መጋቤ ካህናት መ/ር ዕንቁባሕርይ ተከስተ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የካህናት አስተዳደር መምሪያ ሓላፊ እንደተናገሩት “ዛሬ የቅዱሳን ፓትርያርኮችና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መታሰቢያ ቀን ሁሉም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተው ሊያከብሩት ይገባ” ነበር ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ በቅዱሳን ፓትርያርኮችና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መታሰቢያ ቀን ላይ አነስተኛ ሰው መገኘቱ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል፡፡ ብፁዕነታቸው “ዛሬ የምናከብረው የአባቶቻችን መታሰቢያ ቀን ታቦት ወጥቶ ሊከበር ይገባ ነበር፣ ዛሬ ታቦት ይወጣል ቢባል ማንም ሰው አይቀርም ነበር፡፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናት፣ የሰንበት ት/ቤት አባላት በአጠቃላይ ምእመናን ሊያከብሩት የሚገባ በዓል ነበር” በማለት በቁጥር በጣም አነስተኛ ሰው በመገኘቱ ተቆጭተው ተናግረዋል፡፡ “ዛሬ ያከበርነው የአባቶቻችን መታሰቢያ ቀን ነው” ያሉት ብፁዕነታቸው አባቶቻችን የታሰሩበትን፣ የተገደሉበትን ታሪክ ማወቅ አለብን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ፤ የቤተክርስቲያንን አስተዳደር የበለጠ በማጠናከር ልዩ ልዩ ጠቃሚ ተግባራትን ያከናወኑትን፣ ሰበካ ጉባኤ እንዲቋቋም ያደረጉትን በግፍ የገደሏቸው፡፡ ይህ ዛሬ ምን እንዳመጣ እያየን ነው አባቶቻችንን ማሩን ልንል ያስፈልጋል፡፡” ሲሉ አብራርተዋል፡፡ በቀጣይ ዓመት እግዚአብሔር ካደረሰን ሁላችንም፣ ካህናትም፣ ወጣቶችም ተሰባስበን የቅዱሳን ፓትርያርኮችና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን መታሰቢያ ቀን ልናከብር ይገባል ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ምንጭ :- የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/

ተጨማሪ ያንብቡ
፵፭ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ  ጉባኤ

ዜና

፵፭ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ

12 Oct 2026

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፵፭ ኛው አጠቃላይ ዓለም አቀፍ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ዐዲሱ የጽርሐ ተዋሕዶ የስብሰባ ማዕከል ከጥቅምት ፫ - ፯ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ